
ባሕር ዳር: ሰኔ 18/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መሥኮች ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የጤና ሚኒስትር መቅደስ ዳባ (ዶ.ር) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዕውቀት መፍለቂያ አንጋፋ ተቋም ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ለዘመናዊ የጤና ልማት እና የምርምርምር ማዕከል ሞዴል የኾነ ተቋም ስለመኾኑም አንስተዋል።
የዛሬ ተመራቂዎች በሰበሰባችሁት ዕውቀት ሕመም የሚፈውሱ፣ ተቋማትን የሚገነቡ፣ ፍትሕን በማስፈን ኀላፊነት የያዛችሁ ናችሁ ብለዋል። “በሁሉ እሴቶቻችን ሁሉ የተስፋ አምባሳደሮች ሁኑ” ብለዋል።
የኢትዮጵያን የልማት እና የብልጽግና ጉዞ ለማረጋገጥ ተመራቂ ተማሪዎች ምሳሌ መኾን እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
ተመራቂዎች የብዙ ዓመታት ትጋታችሁ ፍሬ አፍርቶ ለዛሬ ቀን በመብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
#አሚኮ #አሚኮዜና #የተማሪዎችምርቃት #ጎንደርዩኒቨርሲቲ #
