“በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን የሚያጎለብቱ የኢንቨስትመንት ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ

4

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀረሪ ክልል የቱሪዝም ዘርፉን የሚያጎለብቱ የኢንቨስትመንት ልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መኾናቸውን የክልሉ ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።

ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ በሀረር ከተማ በመገንባት ላይ ያሉ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን ጎብኝተዋል።

ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ የክልሉ መንግሥት በኢንቨስትመንት አማራጮች ለሚሰማሩ ባለሃብቶች ምቹ ሁኔታዎች መፈጠራቸውን አንስተዋል። በክልሉ ለኢንቨስትመንት ዘርፉ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በተደረገው ጥረትም ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል።

በከተማው በግል ባለሃብቶች እየተገነቡ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችም አበረታች ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። የኢንቨስትመንቶቹ የግንባታ ሥራዎች በታቀደላቸው የጊዜ ሰሌዳ እየተከናወኑ መኾናቸውን ጠቅሰዋል።

ኢንቨስትመንቶቹም የክልሉን የቱሪዝም ዘርፍ የማጎልበት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ጉልህ ፋይዳ እንዳላቸው ገልጸዋል።

በኢንቨስትመንት አማራጮቹ ላይ ተሰማርተው አበረታች ሥራ እያከናወኑ ለሚገኙ ባለሃብቶችም የክልሉ መንግሥት ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

በክልሉ በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ እየታየ የሚገኘው መነቃቃት የበለጠ ለማጎልበት አስፈላጊውን የክትትል እና የቁጥጥር ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።

ባለሃብቶችም የጀመሩትን የግንባታ ሥራቸውን በፍጥነት እና በጥራት አጠናቅቀው ለአገልግሎት ማብቃት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

በጉብኝቱ ላይ የክልሉ ኢንቨስትመንት ቦርድ አባላት እና ሌሎች የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

#አሚኮ_ዜና
#የቱሪዝም_ልማት_ሥራ #በሀረሪ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ከምርጫ ውጭ ላሉ የኃይል አማራጮች ፍላጎት እንደሌለው ያሳየበት ትልቅ እሴት ነው” የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር