
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቡሩንዲ ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ኅብረት የወቅቱ ሊቀመንበር ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ በኢትዮጵያ በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘውን ድል አስመልክተው ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የእንኳን ደስ አለዎት መግለጫ አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንት ኢቫሪስት ንዲያሺሚዬ “የተከበሩ ወንድሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ብልጽግና ፓርቲ በምርጫው ላስመዘገቡት ስኬታማ ውጤት በአፍሪካ ኅብረት እና በቡሩንዲ ሪፐብሊክ ስም የተሰማኝን ልባዊ ደስታ እገልጻለሁ” ብለዋል።
#አሚኮ #አሚኮዜና #PrimeMinister #AbiyAhmed #ኢትዮጵያ
