ለጋ ዕድሜ – ትልቅ ሕልም – ጅምር አበርክቶ

6
ፍኖተሰላም: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በቀላሉ የሚገኙ ቁሳቁሶችን በመጠቀም የበርካቶችን የኑሮ እና የሥራ ጫናን የሚቀይሩ የፈጠራ ሥራዎች በሰፊው ብቅ እያሉ ነው። ይህም የሀገርን ተስፋ በእጅጉ የሚያለመልም ተግባር ነው።
በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተሰላም ከተማ የዳሞት አጠቃላይ ቁጥር አንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ9ኛ ክፍል ተማሪው ወርቅነህ አብቼም በቀላሉ የሚገኙ ቁሳቁሶችን በመጠቀም ለበርካቶች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚችል የዳቦ መጋገሪያ ማሽን በመሥራት የቴክኖሎጅ ሕልሙን በተግባር ገልጧል።
በዳቦ ማምረት ሥራ ለመሰማራት ለማሽን ብቻ በትንሹ ከ70 ሺህ ብር በላይ እንደሚያስፈልግ እና በርካቶች በዋጋው ውድነት ምክንያት ሥራውን ለመጀመር ተግዳሮት እንደኾነባቸው ተማሪ ወርቅነህ ያነሳል።
ይህም በ11 ሺህ ብር ወጭ ብቻ ለንግድ እና ለግል አገልግሎት መስጠት የምትችል የዳቦ መጋገሪያ ማሽን ለመሥራት እንዳነሳሳው ተናግሯል።
ማሽኑ አሁን ላይ በአንድ ጊዜ ሰላሳ ዳቦዎችን መሥራት የሚችል ሲኾን የማሽኑን መጠን በመጨመር የማምረት አቅሙንም ማሳደግ እንደሚቻል ነው ያስረዳው።
ቀጣይ በርካታ ወጣቶች ተጠቃሚ እንዲኾኑ ሥልጠና በመስጠት ወደ ሥራው እንዲቀላቀሉ አልሞ እየተጋ እንደሚገኝም ተማሪው ጠቁሟል።
ሌሎች ችግር ፈቺ የኾኑ የፈጠራ ውጤቶችን እየሠራ እንደሚገኝም ነው ያብራራው።
ተማሪው ከዚህ በፊት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ የፈጠራ ሥራ ውድድሮች ላይ በመሳተፍ ተሸላሚ የነበረ ተማሪም ነው።
ዘጋቢ፦ ንጉሥ ስንታየሁ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት
Next article“የፈጠራ ሥራዎችን መደገፍ እና ዳር ማድረስ ይገባል” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)