
“ኢትዮጵያ ታከናውናለች” በተሰኘው ብሔራዊ ጉባኤ ላይ በመገኘቴ ታላቅ ክብር ይሰማኛል።
“ከለውጥ ወደ ዘላቂ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ላይ፣ በየደረጃው የተጓዝንበትንና አሁን የደረስንበትን መንገድ መለስ ብዬ እንድቃኘው አድርጎኛል።
ሀገራችን በራሷ አቅም ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት፣ ያልተሞከሩ ግዙፍ ልማቶችን በማከናወን በየጊዜው ወደ ላቀ ደረጃ እየተሸጋገረች ትገኛለች።
እነዚህ ሁሉ በአጋጣሚ የተገኙ ድሎች ሳይሆኑ በመደመር መንፈስ ላይ ተመስርተው፣ ዘላቂ ለውጥ የሚመጣው በጋራ በመቆም ነው፤ በሚል ጽኑ እምነት የተወሰዱ፣ በቆራጥ ውሳኔዎች የተገኙ ውጤቶች ናቸው።
የጀመርናቸው ለውጦች በራሳቸው የመጨረሻ ግብ አይደሉም፤ ይልቁንም ከእኛ በኋላ ለሚመጡት ተከታታይ ትውልዶች የምንጥለው ጠንካራ መሠረት ነው።
ሀገርን መገንባት በአንድ ትውልድ ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን የሁላችንም የጋራና ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሆኑ፤ በዚህ ጽኑ እምነት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይህንን መንፈስ ይዞ ወደፊት እንዲጓዝ፣ የተቀበለውን ወረት አግዝፎ ይበልጥ ወደ ላቀ ከፍታ እንዲያመራ ጥሪዬን አቀርባለሁ!
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!



https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
