የአሜሪካ ማዕቀብ ማንሳት እና የቴህራን ማስተባበያ

6
ባሕር ዳር: ሰኔ 16/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአሜሪካ በከፊል ማዕቀብ ማንሳት እና የቴህራን የኒውክለር ፍተሻ ማስተባበያ ስምምነቱን ወዴት ሊያመራው ይችላል?
አሜሪካ እና ኢራን ጦርነታቸውን ለማቆም ባደረጉት አበረታች ንግግር ምክንያት አሜሪካ በኢራን የነዳጅ ኤክስፖርት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ በከፊል አንስታለች።
የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስቴር የ60 ቀናት የማዕቀብ ማቅለያ በመስጠቱም ኢራን ከአስር ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የነዳጅ ዘይቷን በአሜሪካ ዶላር መሸጥ ትችላለች።
የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እስካሁን የተደረገው የሰላም ንግግር ለመጨረሻ ስምምነት ጥሩ መሰረት መጣሉን ገልጸዋል።
ቴህራንም የኒውክሌር ተቆጣጣሪዎችን ወደ ሀገሪቱ እንደምትፈቅድ መናገራቸው ይታወሳል። ኾኖም ኢራን ይህንን የቫንስን ንግግር አስተባብላለች።
የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኒውክሌር ፍተሻዎች ላይ ምንም አዲስ ቃል እንዳልገባ ማመላከቱን ዘ ኢንዲፔንደንት አስነብቧል። ዋና ተደራዳሪው መሐመድ ባገር ቃሊባፍ በበኩላቸው የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በኢራን እየተመራ ለዓለም አቀፍ ሕግ ተገዢ እንደሚኾን እና ለቀጣናው ኢኮኖሚ ብልጽግናን እንደሚመልስ አስታውቀዋል።
ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ሀኪም ጋራ ኢኒሼቲቭን በመደመር መንግሥት ዕይታ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው” ርእሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ