በሰሜን ሸዋ ዞን በሺህዎች የሚቆጠሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

10
🕊
ባሕርዳር: ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላም የሰው ልጅ በምድር ላይ በደስታ እና በነፃነት ለመኖር የሚያስፈልገው መሠረታዊ እና ትልቁ ሀብት ነው። ባለፉት ጥቂት ዓመታት ደግሞ ይህ አስፈላጊ ሰላም በአማራ ክልል ተግዳሮት ገጥሞት ቆይቷል። ይህን ተከትሎም መንግሥት ለታጠቁ ኀይሎች ተደጋጋሚ የሰላም አማራጮችን በማቅረብ እየተቀበለ ይገኛል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ይደሰቱ ክፈተው በ2018 በጀት ዓመት በሺህዎች የሚቆጠሩ የታጠቁ ኀይሎች የሰላምን አማራጭ መቀበላቸውን ተናግረዋል። እነዚህም ከተሀድሶ ኮሚሽን ጋር በመቀናጀት በሦሥት ዙር የመልሶ ማቋቋም ሥልጠና አግኝተው ወደ ማኅበረሰቡ መቀላቀላቸውን አንስተዋል።
አሁን ላይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በኢንዱስትሪ እና በግብርናው ዘርፍ የሥራ ዕድል እንደተፈጠረላቸው ነው የጠቀሱት።
አሁን ላይ መንግሥት እና ሕዝብ ተቀናጅቶ በሠራው ሥራ ዞኑ ከነበረበት የጸጥታ ችግር ወጥቶ አንጻራዊ ሰላም ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ለዚህም የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሉ የጸጥታ መዋቅር፣ የፖለቲካ መሪዎች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ ሰፊ ጥረት አድርገዋል ብለዋል።
አጎራባች ከኾነው የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ጋር ተቀናጅቶ እና ታቅዶ በመሠራቱም ከዚህ በፊት ከነበሩ ጊዜያት የተሻለ ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
የአማራ ሕዝብ ጥያቄ የሚፈታው በኢትዮጵያውያን ጥላ ሥር መኾኑን የገለጹት ኀላፊው ሕዝቡ በተለያየ ጊዜ ችግር ሲያጋጥም ከመንግሥት ጎን በመኾን የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ መሥራቱን አመላክተዋል። የትጥቅ ትግል አዋጭ አለመኾኑን በመረዳት የታጠቁ ኀይሎች መሪዎችን ጨምሮ በየጊዜው የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ እንደኾነም አንስተዋል።
ለአማራ ሕዝብ ሲባል የሰላም አማራጭን መቀበል አዋጭ ነውም ብለዋል። ዞኑ መንግሥት ያስቀመጠውን የሰላም አማራጭ ተከትሎ ለሰላም እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article🕊የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሌሎች የምክክር ሂደቶች በምን ይለያል?
Next articleየደብረ ታቦር ከተማ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሐምሌ ወር ሥራ ይጀምራል።