🕊በምዕራብ ጎንደር ዞን በርካታ የታጠቁ ኀይሎች የሰላምን አማራጭ እየተቀበሉ ነው።

9

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የትጥቅ ትግልን አማራጭ አድርገው በጫካ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ መኾናቸውን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስታውቋል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ደረሰ አዱኛ በ2018 ዓ.ም በርካታ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን መቀበላቸውን ተናግረዋል።

በተሠሩ የፖለቲካ እና የሕዝብ ግንኙነት ሥራዎች እና ታጣቂ ኀይሎች ራሳቸው በሕዝቡ ላይ የሚያደርሱትን ጫና በመገንዘብ የሰላም አማራጭን እየተቀበሉ መኾናቸውን ገልጸዋል።

የታጠቁ ኀይሎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመሥራታቸው እና የመረጡት መንገድ የጥፋት ተልዕኮ የሚፈጸምበት መኾኑን በመረዳት የሰላም አማራጭ መቀበላቸውን አንስተዋል።

🛣በዞኑ ከጎንደር-ገንዳ ውኃ በተደጋጋሚ የሚዘጉ መንገዶች እንዲከፈቱ በማድረግ፣ የመንገዶችን ደኅንነት በመጠበቅ፣ ሰላማዊ የትራንስፖርት ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በኩል የጸጥታ ኀይሉ በትኩረት በመሥራቱ መልካም ውጤት መምጣቱን አብራርተዋል።

ማኅበረሰቡ ከጸጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመሥራት፣ መረጃዎችን በመስጠት፣ የሎጅስቲክ ድጋፍ በማድረግ፣ የሰላም አማራጭ የተቀበሉ ታጣቂዎችን በሰላም በመቀበል ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

🕊በዞኑ አንጻራዊ ሰላም እየሰፈነ መምጣቱን ያነሱት ኀላፊው ይበልጥ ሰላምን ለማጽናት እና ታጣቂዎች የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ ለማድረግ በቀጣይ በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።

#አሚኮ_ዜና #ምዕራብ_ጎንደር #ሰላም #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሂውማን ሄር የጤና ችግር ይኖረው ይኾን?
Next article“ቃል የምንገባቸውን ሁሉ በመፈፀም የተሰጠንን ተጨማሪ የኀላፊነት ጊዜ እንወጣለን ” ከንቲባ አዳነች አቤቤ