ሂውማን ሄር የጤና ችግር ይኖረው ይኾን?

5

 

ባሕር ዳር:ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ሂውማን ሄር/human hair/ በአብዛኛው ሴቶች ለውበት፣ ጸጉር ረዝሞ ወይም በዝቶ እንዲታይ የሚጠቀሙት መዋቢያ ነው። በሠርግ እና መሠል ዝግጅቶች ላይ በስፋት ሴቶች ያዘወትሩታል።

✍️የጤና ችግር ያመጣ ይኾን?

አሜሪካን ኬሚካል ሶሳይቲ ጆርናል የተባለ ተቋም ይሄን በተመለከተ 43 የሂውማን ሄር ምርቶች ላይ ጥናት አድርጎ ባለፈው የካቲት ወር ግኝቱን ይፋ አድርጓል።

በጥናቱ መሠረት ጥናት ከተደረገባቸው 43 የሰው ሰራሽ የጸጉር ምርቶች/human hairs/መካከል በ41 መርዛማ ኬሚካሎች ተገኝተዋል።

✍️ሂውማን ሄር ላይ ኬሚካል ለምን ይጨመራል?

-ጸጉሩ እንዳይቆራረጥ
-ውሃ እንዳያበላሸው
-በተኩስ ወቅት ችግር እንዳያመጣ

✍️ከሚካሎቹ ምን የጤና ችግር ያስከትላሉ?

-በዋናነት ካንሰርን ሊያመጡ ይችላሉ ይላል የአሜሪካን ኬሚካል ሶሳይቲ ጆርናሉ ጥናት። በሂውማን ሄር ላይ እንደሚገኙ በጥናቱ ከተረጋገጡ መርዛማ ኬሚካሎች መካከል 17ቱ ቀጥታ ካንሰር አምጭ ናቸው። የጡት ፣ የደምና የማህጸን ካንሰር ሴሎችን በማባዛት በጊዜ ሂደት ችግር ላይ ይጥላሉ።

-ውፍረት መጨመር
-የስኳር በሽታ
-የነርቭ መዛባት
-የራስ ቅል መቁሰል
የሰውነትን የበሽታ መከላከል አቅም መዳከምን የመሳሰሉ በሽታዎችም ሊመጡ ይችላሉ።

💪መፍትሄ

-አለመጠቀም
-የግድ ከኾነ ከመጠቀም በፊት በደንብ ማጠብ
-ቢያንስ አዘውትሮ አለመጠቀም
-ከምን ከምን እንደተሠሩ ዝርዝር መግላጫ የሌላቸውን ፈጽሞ አለመጠቀም።/ትክክለኛውን ነገር አማራቾቹ ላይጽፉም ይችላሉ/

✍️በእኛ ሀገር ምን ያህል አሳሳቢ ነው?

ሳሙኤል ቦለድ በሀገር በቀል መደሃኒቶች ላይ ጥናት አድራጊ ናቸው። በማኅበራዊ ሚዲያ ደግሞ ዓለም አቀፍ ጥናቶችን ጨምሮ መረጃ ያሠራጫሉ።
አሜሪካን ኬሚካል ሶሳይቲ ጆርናል ያጠናውን ሂውማን ሄር በጤና ላይ የሚያመጣውን ችግርም በማኅበራዊ ሚዲያ ተንትነዋል።

-በጥናቱ የተጠቀሱ የጸጉር ምርቶች ለአፍሪካውያን ሴቶች ተብለው እና አሜሪካና አውሮፓ የማይሸጡ ናቸው አሉ አቶ ሳሙኤል።

ይሄም የምርቶቹን ጤነኝነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባል ባይ ናቸው። ጥናቱ ላይም በይፋ ጥቁር ሴቶችን ታሳቢ ተደርገው እንደሚመረቱ ተገልጿል።

-በእኛ ሀገር ምርቶቹ የሚያደርሱትን ጉዳት በተመለከተ መረጃ የማግኘት ውስንነት ስላለ አሳሳቢ እንደሚያደርገውም ገልጸዋል።

መርዛማ ኬሚካሎቹ በቆዳ በኩል አድርገው ወደ ደም ስር የሚገቡ ሲኾን ተጠቀሚዎቹ ብቻ ሳይኾን ጸጉር ሠሪዎቹም ላይ ጉዳት ሊያመጡ ይችላሉም ብለዋል።

በተረፈ በሀገር ውስጥ ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ነው አቶ ሳሙኤል ቦለድ የገለጹት።

💪”ማጌጥ በራስ፣ ሲያጌጡ እንዳይመለጡ” እንዲሉ!

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአሚኮ ቤተሰቦች ቀን ተከበረ።
Next article🕊በምዕራብ ጎንደር ዞን በርካታ የታጠቁ ኀይሎች የሰላምን አማራጭ እየተቀበሉ ነው።