የአሚኮ ቤተሰቦች ቀን ተከበረ።

8

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአሚኮ የመጀመሪያው የቤተሰቦች ቀን በተቋሙ የሚሠሩ ባልደረባዎች ልጆች በተገኙበት ተከብሯል።

የአሚኮ ቤተሰቦች ቀንን ያስጀመሩት የአሚኮ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ ወላጆች እና ሕጻናት በዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሚኮን ቤተሰቦች ቀን በደማቅ ሥነ-ሥርዓት እንዲከበር በማድረጋቸው ምሥጋና አቅርበዋል።

የአሚኮ ቤተሰቦች ቀን ቤተሰባዊነትን የሚያጎለብት በመኾኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አሥፈጻሚው ገልጸዋል። እንደዚህ አይነት ጠንካራ መስተጋብሮች አሚኮን በማወቅ እና በማሳወቅ ረገድ ትልቅ ጉልበት እንዳላቸውም ተናግረዋል።

የበዓሉ ተሳታፊ ወላጆች የቀኑ መዘጋጀት አብሮነትን በማስረጽ ልዩ ቤተሰባዊነት እና አንድነትን ፈጥሮልናል፤ ለእርስ በእርስ ትውውቅም በር ከፍቷል ብለዋል።

በመርሐ ግብሩ በአሚኮ ሁሉንአቀፍ ጉብኝት ተካሂዷል።

#አሚኮ_ዜና #የአሚኮ_ቤተሰብ_ቀን #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጤናማ እና ዘመናዊ የፖለቲካ ባሕል የማዋለድ ተግባራችንን በተጠናከረ መልኩ እንቀጥላለን” ኢዜማ
Next articleሂውማን ሄር የጤና ችግር ይኖረው ይኾን?