
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ጉዞ እንዲሳካ ድጋፉን እንደሚቀጥል የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል።
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በታዛቢነት የተሳተፉት የአፍሪካ ኅብረት የፖለቲካ ጉዳዮች ሰላም እና ደኅንነት ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዶዬ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የሚባል ምርጫ ማድረጓን ገልጸዋል። መንግሥት የምርጫ ቦርድ ነፃ እና ገለልተኛ እንዲኾን የሠራውን ሥራ አድንቀዋል።
የአፍሪካ ኅብረት በገለልተኝነት ዴሞክራሲያዊ መንግሥት እና ተቋማት እንዲመሠረቱ የሚደረገውን ሂደት ይደግፋል ነው ያሉት።
ኢትዮጵያ የሕግ የበላይነትን ባከበረ መንገድ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማካሄዷን ገልጸዋል። የአፍሪካ ኅብረት ለአካታች እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የጀመራቸውን ጥረቶች አጠናክሮ በቁርጠኝነት ይሠራል ብለዋል።
ኅብረቱ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አና መንግሥት ጎን በመቆም ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር መዳበር የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ነው ያሉት።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #አፍሪካ_ኅብረት
ዘጋቢ: ቤቴልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
