ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በዴሞክራሲያዊ ሂደት እንዲሳተፉ አዲስ ልምምድን ፈጥሯል።

4

 

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በታዛቢነት በተሳተፈባቸው 136 ምርጫ ክልሎች ሴቶች ያለስጋት ደኅንነታቸው ተጠብቆ መሳተፋቸውን እና ምርጫው ሰላማዊ እንደነበር አስታውቋል።

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ኅብረት አባሆይ ማኅበሩ ከምርጫ ቦርድ እና ከሌሎች የሀገር ውስጥ እና የውጭ የሲቪክ ማኅበራት ጋር ጥምረት ፈጥሮ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል።

ሴቶች በምርጫ ሂደት ወቅት የሚያጋጥማቸውን ጾታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለመከላከል መመዘኛ አውጥቶ ሠርቷል ነው ያሉት። በዚህም 98 በመቶ የሚኾነው የምርጫ ሂደት በግልፀኝነት እና ሰላማዊ ኾኖ የተካሄደ እንደነበር ተናግረዋል።

በጋራ በተገነቡ ሥርዓቶች ውስጥ ችግሮችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የሲቪክ ማኅበራት ሚናችንን በአግባቡ መወጣት አለብን ነው ያሉት።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች በዴሞክራሲያዊ ሂደት መብታቸው ተጠብቆ እንዲሳተፉ ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ገልጸዋል።

#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ጠቅላላ_ምርጫ #ሴቶች #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ: ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የውጤት ማሳወቂያ መርሐግብር እያካሄደ ነው።
Next article“ኢትዮጵያ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማትን እየገነባች ነው” የአፍሪካ ኅብረት