
አዲስ አበባ፡ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሠብሣቢ ሜላተወርቅ ኀይሉ መርሐ ግብሩ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ብቻ ሳይኾን የተመዘገቡ ተቋማዊ ለውጦችን እና በሂደቱ ያጋጠሙ ችግሮችን ለተሳታፊዎች የምናሳውቅበት ነው ብለዋል።
ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የቅሬታ አፈታት ሂደቱን የማቀላጠፍ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሕጋዊ መሠረት እንዲኖረው የማድረግ፣ የሴቶች እና አካል ጉዳተኞችን የፓለቲካ ተሳትፎ በአካታችነት በመተግበር ረገድ ጠንካራ ሥራዎችን መሥራቱንም ገልጸዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የዲጂታል ምዝገባም ከ5 ሚሊዮን በላይ መራጮች በዲጂታል መንገድ እንዲመዘገቡ አስችሏል ነው ያሉት።
ቦርዱ ተቋማዊ ገለልተኝነቱን አስጠብቆ ሕግን ብቻ ተከትሎ ለመሥራት በቁርጠኝነት መንቀሳቀሱንም ጠቁመዋል። ያልተገቡ ጣልቃ ገብነቶችን ለመከላከልም ቦርዱ ውሳኔዎችን በግልጽ እና በተጠያቂነት ስሜት ሲያከናውን መቆየቱንም ነው ሠብሣቢዋ ያነሱት።
በመርሐግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴን ጨምሮ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የዴሞክራሲ ተቋማት መሪዎች፣ የመገናኛ ብዙኅን ኀላፊዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እና በምርጫ ሂደቱ የተሳተፉ ልዩ ልዩ ታዛቢዎች ተገኝተዋል።
#አሚኮ_ዜና #7ኛው_ምርጫ_2018 #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ: ቤተልሄም ሰለሞን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
