“ኢቦላ በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ ቢኾን ኖሮ እስካሁን ክትባት እና መድኃኒት ይሠራለት ነበር” ዶክተር ዣን ካሴያ

3

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል አህጉሪቱ ለኢቦላ ምላሽ የራሷን በጀት መመደብ ይኖርባታል ብሏል።

አሁን ላይ የተከሰተው ወረርሽኝ የ200 በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል፤ 900 የሚጠጉ ሰዎችም በቫይረሱ ተይዘዋል ነው ያለው።

የወረርሽኙ መኖር በይፋ የተረጋገጠው ዘግይቶ ነው፤ እውነተኛው የተጠቂዎች ቁጥር ከተጠቀሰው በላይ ሊኾን እንደሚችል አፍሪካ ኒወረስ የዜና ወኪል አስነብቧል።

ለአሁኑ የቦንዲቡግዮ ቫይረስ የጸደቀ ክትባትም ኾነ መድኃኒት አለመኖሩ ወረርሽኙን ለመግታት ትልቅ ፈተና ኾኗል ነው የተባለው።

የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጂን ካሴያ ይህ ወረርሽኝ በአውሮፓ ወይም በአሜሪካ ቢኾን ኖሮ እስካሁን ክትባት እና መድኃኒት ይሠራለት ነበር ብለዋል። በሽታው የነሱ ባለመኾኑ ፍላጎት የላቸውም፤ ይህ ደግሞ አፍሪካውያን ራሳቸውን ለመንከባከብ እና ክትባት ለማምረት እንዲነቁ ያደርጋል ብለዋል።

የኮረና ወረርሽኝ በአፍሪካ የክትባት ምርትን ለማሳደግ ጥረት ቢያስጀምርም እስካሁን የተገኘው ውጤት ግን አነስተኛ እንደኾነ ጠቁመዋል።

ክትባቶችን ለማፋጠን ጥረቶች ቢኖሩም እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ዝግጁ የኾነ ክትባት ስለመኖሩ እርግጠኛ እንዳልኾኑ ካሴያ ገልጸዋል።

#አሚኮ_ዜና #ጤና_ኢቦላን_መከላከል #አፍሪካ

በስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕገ ወጥ የአፈር ማዳበሪያ ዝውውርን ለመከላከል በቅንጅት እየተሠራ ነው።