የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልእክት!

2

 

የሀገራችንን ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማፋጠን፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የብልጽግናችንና የኢኮኖሚ ዕድገታችን ዋና ምሦሶ አድርገናል።

ለዚህ ስኬት ደግሞ መንግሥታችን በቀረጸው የትምህርት ፖሊሲ በመታገዝ ብቃት ያለው፣ የፈጠራ ክሂሎት የተላበሰና ምርታማ የሰው ኃይል ለመገንባት በትጋት እየሠራ ይገኛል።

ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተን የ2018 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎችን ያስመረቅንበት ሥነ ሥርዓት፣ በሳይንስና ፈጠራ የላቀ ዕውቀትን የሰነቁ የለውጥ መሐንዲሶቻችን ወደ አዲስ የሥራና የፈጠራ መስክ የተሻገሩበት አዲስ ምዕራፍ ነው።

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የፈጠራ ማዕከላትና የለውጥ ሞተሮች በመሆን ለሀገራችን ችግሮች ምላሽ የሚሰጥ ምርምር የማካሄድ እና ለአካባቢያችን ተስማሚ ቴክኖሎጂዎችን የማልማት ትልቅ ኃላፊነት ያለባቸው ሲሆን፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ በዚህ ረገድ የጀመረው ስኬታማ ጉዞ በእጅጉ የሚበረታታ ነው።

የተማረ ወጣት ኃይላችን በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ሊያሳየው የሚገባው የፈጠራ ቁርጠኝነት እና የሳይንስ ብስለት፤ በሀገራችን የዲጂታል ሽግግርና የልማት ጉዞ ላይ የተጋረጡ የኋላቀርነት ማነቆዎችን ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ የሚያስችል ትልቅ ዐቅም ነው።

መንግሥት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ተመራቂ ባለሞያዎች ሁልጊዜም ቢሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ። ለተመራማሪዎችም ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠሩ ረገድ ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል።

Previous articleበአፍሪካ የመጀመሪያ የኾነው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ እውን ሊኾን ነው።
Next articleየ403ኛ ኮር በአስቸጋሪ ወቅትም ፈተናን ተቋቁሞ በጽናት በማለፍ አርዓያነት ያለው ተግባር መፈጸም የቻለ ሠራዊት ነው።