📱🇪🇹ኢትዮጵያ በዲጂታሉ ዓለም ወደ ላቀ ደረጃ እየተሻገረች ነው።

2

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) መንግሥት ለዘመናዊ አሠራር ቅድሚያ በመስጠት የመንግሥት አገልግሎትን ወደ ዲጂታል አሠራር እየቀየረ ይገኛል።

ይህ የዲጂታል አሠራር ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት የሚያባክኑትን ጊዜ እና ጉልበት በማስቀረት፣ ብልሹ አሠራር እንዲታረም በማድረግ፣ የደንበኞችን የፋይል መጥፋት በማስቀረት፣ ቀልጣፋ እና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት እንዲሰጥ በማድረግ ጠቀሜታው የጎላ ነው።

በሀገር ደረጃ በዲጂታል የታገዘው ሞሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ደግሞ በአንድ ማዕከል በርካታ አገልግሎቶችን በመስጠት፣ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት በመስጠት ዜጎች በያሉበት አገልግሎቱን እንዲያገኙ በማስቻል እና ብልሹ አሠራርን በማስቀረት ዜጎች ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ ነው።

ይህም ኢትዮጵያ በዲጂታሉ ዓለም ከአፍሪካ ቀዳሚ ለመኾን እያደረገች ያለውን ስኬታማ ጉዞ የሚያሳይ ነው።

የኢትዮጵያ የዲጂታል አገልግሎት አብዮት የተቀጣጠለ ሲኾን ባንኮች አገልግሎታቸውን ዲጂታላይዝድ በማድረግ ደንበኞች በየትኛውም ቦታ ኾነው ገንዘብ እንዲላላኩ እና እንዲያዘዋውሩ በማድረግ ፈጣን አገልግሎት እንዲሰጡ አስችሏቸዋል።

ባንኮች ከፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ጋር በማገናኘት የደንበኛን አሥተማማኝ የባንክ ደኅንነትን ለመጠበቅ የዲጂታል አገልግሎትን እየተጠቀሙ ይገኛሉ።

ለኢትዮጵያ የዲጂታል ዕድገት ሌላው ማሳያ ደግሞ የኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ግብይት ነው።

በዲጂታል አገልግሎት ዘርፍ ስኬታማ ጉዞን እያከናወነ የሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም በቴሌ ብር ዲጂታል ግብይት በዓመት 2 ነጥብ 38 ትሪሊዮን ብር በላይ ገቢ እንደሚያገኝ የተቋሙ መረጃ ያሳያል።

ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት በስድስት ወር ውስጥ ከቴሌ ብር የሞባይል መድረኮች 4 ነጥብ 1ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘት ችሏል። ይህም ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን ጉልህ ሚና እንዲወጣ አድርጎታል።

መንግሥት ለዲጂታል አገልግሎት የሰጠው ትኩረት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድትኾን የሚያስችላትም ነው።

በተለይም በሀገሪቱ የተስፋፋውን ብልሹ አሠራር የሚቀይር፣ ዜጎች አገልግሎት ለማግኘት የሚደርስባቸውን እንግልት የሚያስቀር፣ የሀገር ድኅንነት በዲጅታል ሥርዓት እንዲጠበቅ የሚያስችል፣ በውጭ ኢንቨስተሮች ተመራጭ እንድትኾን በር የሚከፍት ነው።

#አሚኮ_ዜና #የዲጂታል_አገልግሎት #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሳይንስ ሙዚየም የኢትዮጵያ ዲጂታል ከፍታ አብሳሪ ነው።
Next articleበአፍሪካ የመጀመሪያ የኾነው የኤ.አይ ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ እውን ሊኾን ነው።