“መንግሥት ለስፖርት ልማት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው” ባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር

3

 

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የባሕል እና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዓመቱ በስፖርት ልማት ዘርፍ በርካታ ታላላቅ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል።

መንግሥት ለስፖርት ልማት ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን የተናገሩት ሚኒስትሯ በአሁኑ ወቅት ከ45 ሺህ በላይ የስፖርት ማዘውተሪያዎች መገንባታቸውን ተናግረዋል።

በቀጣይም ታላላቅ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ የሚችሉ ስታዲየሞችን ለማጠናቀቅ እና የስፖርት ማዘውተሪያ ቦታዎችን ይበልጥ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

በባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መክዩ መሐመድ ስፖርትን ከውድድር ባለፈ ለሀገር ልማት እና ዕድገት መሠረት እንዲኾን ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑን ገልጸዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው በ2018 ዓ.ም በዓለም መድረኮች ከመሳተፍ ባለፈ ታላላቅ የዓለም እና አህጉር አቀፍ ውድድሮችን ኢትዮጵያ ማስተናገድ የቻለችበት እንደነበርም ተናግረዋል። ይህም ለሀገር ገጽታ ግንባታ እና ለዲፕሎማሲ ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበረው አንስተዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባሕል እና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ወርቅሰሙ ማሞ፣ በቅርቡ የጸደቀውን አዲሱን የስፖርት ልማት እና አሥተዳደር አዋጅ በሚገባ ለመተግበር ባለድርሻ አካላት ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።

በመድረኩ የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴርን ጨምሮ ሁሉም ፌዴሬሽኖች በ2018 ዓ.ም በስፖርት ልማት ዘርፍ የሠሩት የተግባር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሎ ይጠበቃል።

#አሚኮ_ዜና #ስፖርት_ልማት #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ባዘዘው መኮንን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት የተገነባው የጭና ሰማዕታት መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ለአገልግሎት በቃ።
Next article“በቴክኖሎጅ ዘርፍ በአጭር ጊዜ ያመጣነውን ለውጥ ለአፍሪካ ምሳሌ ኾነን ዓድዋን ዳግም በልማት እናሳያለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)