
ጎንደር: ሰኔ 13/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር መከላከያ ሠራዊት 403ኛ ኮር የተገነባው የጭና ሰማዕታት መታሰቢያ ጤና ጣቢያ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ የምትገኘው የጭና ቀበሌ በወርሐ ነሐሴ 2013 ዓ.ም ለሀገር ሉዓላዊነት የሕይወት መስዋዕትነት የተከፈለባት ምድር ናት።
በጦርነቱ ወቅት በጭና የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ የጸጥታ አካላት፣ ወጣቶች፣ እናቶች እና ሴቶች ለሀገራቸው ዘብ ቆመው ዋጋ ከፍለውባታል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሀገርን ዳር ድንበር ከመጠበቅ ባለፈ የማኅበረሰቡን ችግሮች በመለየት ተጠቃሚ እንዲኾኑ እየሠራ መኾኑ በምርቃቱ ወቅት ተገልጿል።
በምረቃ መርሐ ግብሩ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መሪዎች፣ የክልል እና የዞን የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
#አሚኮ_ዜና #የጤና_ጣቢያ_ግንባታ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ
ዘጋቢ:-ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
