የቀጣናው የኢኮኖሚ ሞተር ኢትዮጵያ!

5
⚡🛤
ባሕር ዳር: ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማረጋገጥ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በማሳደግ ውጤታማ ሥራ እየሠራች ነው።
🌆 ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ሀገራት በኤሌክትሪክ ኀይል ፣ በወደብ አማራጭ፣ በትራንስፖርት እና መሰል የመሠረተ ልማት እና በተለያዩ ዘርፎች ትስስሯን በማሳደግ ላይ ናት።
የዓባይ ግድብን በስኬት በማጠናቀቅ የአይቻልምን መንፈስ በመስበር አፍሪካውያን ማንኛውንም ሥራ በራሳቸው አቅም ማድረግ እንደሚችሉ ኢትዮጵያ በስኬት በማጠናቀቅ ማሳየቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአሁን ቀደም መናገራቸው ይታወሳል።
ለኬኒያ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን ኢትዮጵያ ለዓመታት የኤሌክትሪክ ኀይል ስታቀርብ ቆይታለች። ይህም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ ከማስገኘቱም በላይ የጎረቤት ሀገራትን የኀይል እጥረት ቀርፏል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኀይል የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሞገስ መኮንን ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኃይል ማመንጫ አቅሟን እና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን በከፍተኛ ሁኔታ አስፍታለች።
ብሔራዊ የኤሌክትሪክ አቅርቦትንም በከፍተኛ ሁኔታ ጨምራለች። እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ አይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት እና የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ያሉ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች አቅምን በማሳደግ ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል።
ባለፉት ዘጠኝ ወራት ኤሌክትሪክን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 366 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ተገኝቷል። ይህም ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ138 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳይቷል ነው ያሉት
በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል የተዘረጋው የ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኀይል ማስተላለፊያ መስመር በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ መግባቱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ገቢ አድጓል። ኬንያም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፏን የሚደግፍ አስተማማኝ ኀይል አግኝታለች።
🛤ሌላኛው የኢትዮጵያ -ጂቡቲ🚉 የባቡር መስመር የኢትዮጵያን የወጭ እና ገቢ ንግድ በማሳለጥ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው።
ኢትዮጵያ በቀጣናው እያደረገች ያለው ጠንካራ የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴ የውጭ ኢንቨስተሮችን በመሳብ ፍሬ እያፈራ ይገኛል።
በቅርቡም የነዳጅ፣ የማዳበሪያ፣ የኒውክሌር ማብለያ ፍብሪካዎችን በማስጀመር የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማሰለጥ እየሠራች ነው።
ዘጋቢ:-ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleታላቁ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ኘሮጀክት የኢትዮጵያ የመቻል ማሳያ ነው።
Next articleየምድርን ጤና ከመጠበቅ አልፎ የምግብ ሉዓላዊነትን እስከማረጋገጥ የገዘፈው የአረንጓዴ አሻራ ጉዞ