በጎንደር ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎች ለከተማዋ ውበትን የጨመሩ ናቸው።

7
ጎንደር: ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በጎንደር ከተማ እየተሠራ ያለውን የዞብል ፓርክን የሥራ ሂደት ተመልክተዋል።
በመስክ ምልከታው የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይረጋ ሲሳይ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የከተማ እና መሠረተ ልማት ሥራ አሥኪያጅ ሙሉጌታ ታደስ በጎንደር ከተማ በኮሪደር ልማት እየለሙ ከሚገኙ ቦታዎች መካከል አንዱ የኾነው የዞብል ፓርክ 5 ነጥብ 1 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ መኾኑን ገልጸዋል።
ግንባታው የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የንግድ ተቋማት፣ ሁሉንም ማኅበረሰብ ያማከለ መዝናኛ ቦታዎች እና የመኪና መቆሚያ ያካተተ መኾኑንም አንስተዋል።
ፕሮጀክቱ በቅርቡ ተመርቆ አገልግሎት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ አማኑኤል ፈረደ (ዶ.ር) የመስክ ጉብኝቱ ልዩ ስሜት እንደፈጠረባቸው ገልጸዋል።
የኮሪደር ልማቱ ከአሁን በፊት ያልታዩ የከተማዋን ታሪካዊ ቦታዎች በማልማት ለማኅበረሰቡ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት የሚያሳይ መኾኑንም ተናግረዋል።
የዞብል ፓርክ በየዓመቱ የጥምቀተ ባህሩ ከሚከበርበት ቦታ ጎን መገንባቱ ለከተማዋ ውበት ከመጨመር ባለፈ የጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የጎላ መኾኑንም ገልጸዋል።
በጎንደር ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባውም አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ፦ ማኅደር አድማሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከገናና የሰማይ ላይ ስም እስከ ቅንጡ የምድር ላይ ክብር!
Next articleታላቁ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ኘሮጀክት የኢትዮጵያ የመቻል ማሳያ ነው።