የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሕዝቡን የጤና ተጠቃሚነት የሚያረጋገጥ የሪፎርም ሥራ እያከናወነ ነው።

3

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ​የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በጤና አገልግሎት እና አሥተዳደር ሪፎርም ትግበራ ሂደት ላይ የሚመክር ውይይት አካሂዷል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ የአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ ሁለንተናዊ እና ሀገር በቀል የሪፎርም ትግበራ እየተከናወነ ነው።

እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ መከላከልን ብቻ መሠረት አድርጎ የነበረውን የጤና ፖሊሲ አሁን ላይ መከላከልን እና ማከምን ጎን ለጎን አጣምሮ በመያዝ ለላቀ ስኬት ጠንካራ መሠረት ለማስቀመጥ በትኩረት እየተሠራ ነውም ብለዋል።

በስትራቴጂ እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተው ይህ ግብ ተኮር ሪፎርም የሕዝቡን የጤና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ቁልፍ የኾኑ ትኩረቶችን ስለማንገቡም ጠቁመዋል። ይኸውም ማኅበረሰቡ ፍትሐዊ እና ጥራት ያለው አገልግሎት በፈጣን ሁኔታ እንዲያገኝ ያስችላል።

የሀገር ውስጥ ሀብትን በማሠባሠብ የጤናውን ዘርፍ ከጥገኝነት የሚያላቅቅ ዘላቂ የፋይናንስ ሥርዓት መገንባት፣ ዲጂታል አሠራርን መተግበር የሪፎርሙ ግቦች መኾናቸውንም ገልጸዋል።

ሰፊው የለውጥ ጉዞ በዝግጅት፣ በትግበራ እና በማጽናት የተከፋፈሉ ሦሥት ዋና ዋና ምዕራፎች እንዳሉትም ጠቁመዋል። በአሁኑ ወቅት የዝግጅት ምዕራፍ ሥራዎች በተሳካ ሁኔታ እየተከናወኑ ነው ብለዋል።

የትግበራ ምዕራፉንም ከሐምሌ ወር በኋላ ለመጀመር ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል። ሪፎርሙ የዕለት ተዕለት ጥቃቅን ጉዳዮችን ብቻ ሳይኾን የክልሉን መንግሥት የ25 ዓመት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ የትውልድ ዕቅድን የሰነቀ ነው ብለዋል።

በመኾኑም መሪዎች እና ባለሙያዎች ስትራቴጂካዊ በኾኑ ትላልቅ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ጥልቅ የእሳቤ እና የተግባር ለውጥ ሊያመጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #የጤና_አጠባበቅ_ሥራ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች
Next article“ዝግባ የሕጻናት እና አረጋውያን መርጃ በጎ አድራጎት ድርጅት እርስ በእርስ መረዳዳትን ያሳየ ነው” አቶ ጎሹ እንዳላማው