በደቡብ ወሎ ዞን ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እየተከተሉ ነው።

8

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከሰላም እጦት ወጥቶ ሕዝቡ በነጻነት እንዲንቀሳቀስ፣ የልማት ሥራዎች እንዲፋጠኑ እና መሠረታዊ አገልግሎቶች ያለምንም መስተጓጎል እንዲካሄዱ መንግሥት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪዎችን አድርጓል፤ እያደረገም ነው።

በርካታ ታጣቂዎችም ለሕዝብ እና ለሀገር ሲሉ የሰላም አማራጭን በመቀበል ወደ መደበኛ ሕይወታቸው እየተመለሱ ነው።

እየተጠናቀቀ በሚገኘው የ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት በደቡብ ወሎ ዞንም ቁጥራቸው በርከት ያሉ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተከትለው መግባታቸውን የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ዘለቀ አለባቸው አስታውቀዋል።

እነዚህ ወጣቶች ጦርነት እና የጥፋት መንገድ ሀገርን የሚያፈርስ እንጂ ለማንም የማይጠቅም መኾኑን በመረዳት ወደ ሰላም አማራጭ መምጣታቸውን ተናግረዋል።

ታጣቂዎች የተሀድሶ ሥልጠና ወስደው በተለያዩ የገቢ ማስገኛ የልማት ሥራዎች መሰማራታቸውንም ጠቁመዋል።

ተመላሾችን በበቂ ሁኔታ መልሶ የማቋቋም፣ የሥራ ዕድል የመፍጠር እና የመደገፍ ሂደት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል።

የጸጥታ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ማኅበረሰቡ የሰላሙ ባለቤት እንዲኾን ትኩረት መሰጠቱን ረዳት ኮሚሽነር ዘለቀ አለባቸው ተናግረዋል። ለዚህም ወጣቶችን፣ እናቶችን፣ ሴቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን የማደራጀት ሥራ እየተከናወነ ይገኛል።

ዋና ዓላማውም በስህተት መንገድ ላይ ያሉ ወጣቶችን ማስተማር እና ማስገንዘብ ነው። በዚህም ወጣቶቹ ወደ ቀደመ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እና የጥፋት መሣሪያ እንዳይኾኑ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

#አሚኮ_ዜና #ወደሰላም_የተመለሱ_ታጣቂዎች_በልማት_ሥራ_ማሰማራት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ጥያቄዎችን ለመመለስ በቁርጠኝነት እየተሠራ ነው።