
ባሕር ዳር: ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሀረሪ ክልል አሥተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የ2018 የበጀት ዓመት የ11 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም መነሻ በማድረግ የቀረበለት የበጀት ክለሳ አጽድቋል።
ካቢኔው በክልሉ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ አማካኝነት የቀረበለትን ከ301 ሚሊዮን 693 ሺህ 178 ብር የበጀት ክለሳ ነው ተወያይቶ ያጸደቀው።
የበጀት ክለሳው ያስፈለገው በተለይም የፊዚካል እና ፋይናንሻል አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የኾኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት የላቀ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳ ላላቸው እና የበጀት እጥረት ላጋጠማቸው ጉዳዮች የሚውል ነው ተብሏል።
የበጀት ክለሳ አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ የኾኑ ፕሮጀክቶችን በመለየት እና በመከለስ የቅድሚያ ቅድሚያ ለተሰጣቸው ተግባራት የሚውል መኾኑም ተመልክቷል።
ካቢኔውም የቀረበለትን የበጀት ክለሳ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። ካቢኔው በተጨማሪም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ አቅጣጫ አስቀምጣል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
