
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ለምርትና ምርታማነት ትልቅ ድርሻ ያለውን የአፈር ማዳበሪያ በሀገር ውስጥ በማማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን ሀሴት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረቻ ፋብሪካ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር መላኩ አለበል ጎብኝተዋል።
የተፈጥሮ ማዳበሪያ በማምረት ወደ ሀገር ውስጥ ገበያ ለማስገባት በሂደት ላይ ያለውን ፋብሪካ የአመራረት ሂደት እና የምርት ጥራት የተመለከቱት ሚኒስትሩ ፤ ሀገራችን ከያዘችው በርካታ ወጪ የሚወጣበትን ሰው ሠራሽ የአፈር ማዳበሪያ በተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ ለመተካት እንደ ሀገር እየተሠራ ያለውን ሥራ ሊያግዝ የሚችል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በተለይም በሀገራችን መመረቱ የማዳበሪያ አቅርቦትና ስርጭት በወቅቱና በሰዓቱ በሚፈለገው መጠን ለአርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሩ ተደራሽ እንዲሆን ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ያሉት ሚኒስትሩ፤ የአፈርን ለምነት በመጠበቅ ታክሞ ለረጅም ጊዜ ለምነቱን እንዲጠብቅ እና የምርት ጥራት በመጨመር ከፍተኛ ምርት እንዲገኝ የሚያስችል ማዳበሪያ መሆኑን ገልፀዋል።
በቀጣይም ምርቱን በስፋት በማምረትና በማስተዋወቅ ለገበያ ተደረሽ እንዲሆን መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ሀሴት የተፈጥሮ ማዳበሪያ ማምረቻ ሥራ አስኪያጅ ሄኖክ ስሞን በበኩላቸው የተፈጥሮ ማዳበሪያ በግብርና ሚኒስቴር ላቦራቶሪ እና በኢትዮጵያ ደረጃዎች ተቋም ጥራቱን የማረጋገጥ ሥራዎች ተጠናቀዋል ብለዋል ፡፡
ፍብሪካው ውጤታማነቱን በማረጋገጡ በቅርብ ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ያጠናቀቅ ሲሆን በቀን ከአንድ መቶ ሺህ በላይ ኪሎ ግራም ማዳበሪያ በማምረት ለ85 ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል ፡፡ መረጃው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ነው።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #ለሁለንተናዊ_ሉዓላዊነት #እኛም_እንሸምት
#MadeInEthiopia
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
