🕊የሰላም ተስፋው በዓለም የኢኮኖሚ መረጋጋት እና በነዳጅ ዋጋ ላይ በጎ ተጽዕኖ ፈጥሯል።

3

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ እና በኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ሮይተርስ ዘግቧል። ይህ የዋጋ ቅናሽ ባለፉት ሦሥት ወራት ታይቶ አይታወቅም።

የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሚል 81 ነጥብ 47 ዶላር ኾኖ ተመዝግቧል። የአሜሪካው ማጣቀሻ ነዳጅ ደግሞ ወደ 78 ነጥብ 86 ዶላር ዝቅ ብሏል።

የነዳጅ ዋጋው ቢቀንስም አሁንም ከጦርነቱ በፊት ከነበረው ደረጃ ከፍ ያለ እንደኾነ ተመላክቷል።

ሁለቱ ሀገራት የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ በመጭው ዓርብ በስዊዘርላንድ ይፈራረማሉ። ስምምነቱ የተዘጋውን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በድጋሚ ለመክፈት ዕድል ይሰጣል። ነገር ግን የባሕር ፈንጂዎችን የማጽዳት ሥራ መደበኛውን የነዳጅ ትራፊክ በጥቂት ሳምንታት ሊያዘገየው እንደሚችልም ተጠቁሟል።

አሜሪካ የባሕረ ሰላጤውን ኤክስፖርት ለማስቀጠል በስውር ነዳጅ ስታወጣ መቆየቷ ተጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የዓለማችን ትልቁ የነዳጅ አስመጭ የኾነችው ቻይና የነዳጅ ፍላጎቷ ቀንሷል። የቻይና ፍላጎት መቀነስ እና የኢራን ነዳጅ ወደ ገበያው መመለስ በገበያው ላይ ተጨማሪ የዋጋ ቅናሽ ግፊት ፈጥሯል ነው የተባለው።

የስምምነቱ ሙሉ ዝርዝር ስላልተለቀቀ በነዳጅ ገበያው ላይ የዋጋ መለዋወጥ ስጋት አሁንም እንዳለ ዘገባው ጠቁሟል።

#አሚኮ_ዜና #የአሜሪካ_ኢራን #የሰላም_ስምምነት #በነዳጅ_ገበያ #ያመጣው_በጎ_ተጽኖ

ዘጋቢ:- ስማቸው አጥናፍ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🕊በሰሜን ጎጃም ዞን ከ500 በላይ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።
Next articleሕጻናትን አሳታፊ እና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሥራዎች እየተሠሩ ነው።