
ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ እና በአሁኑ ሰዓት ሰላምን መርጠው የተመለሱ አካላትን የምክክር አጀንዳ ተረክቧል።
በአጀንዳ ርክክብ መድረኩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ፤ ብቸኛው የሰላም መንገድ ምክክር መሆኑን አምናችሁ በመምጣታችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል።
አክለለውም ከጥቅ ትግል የሰላም ትግል መርጣችው በመመምጣታችሁ በውሳኔአችሁ ልትኮሩ ይገባል በማለት አድናቆታቸውን ገልፀዋል ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረስላሴ።
ኮሚሽኑ የተረከበውን አጀንዳ በቅርቡ የሚያካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አካል እንደሚያደርገውም ገልፀዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
