ከሰሞኑ በማኅበራዊ ሚዲያ የወላይታ ዩኒቨርስቲ ተማሪው በሚል ስለሚዘዋወረው መረጃ እናቱ ምን አሉ?

8

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 09/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ከታች በምስሉ የሚታየው ወጣት ባንተ ዓለም ሰይድ እንደሚባል፣ የባሕር ዳር ልጅ እና የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ እንደሚል፤ የጤናና መሰል ችግር ያለበት መኾኑን በስፋት በማኅበራዊ ሚዲያ ተሠራጭቷል።

ወጣቱ ከቤተሰቡ ጋር እንዲገናኝ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለትም ጥሪዎች ቀርበዋል።

ስለ ወጣቱ በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨው እውነት ነውን!

አሚኮ እውነታ ማጣሪያ እናቱን በስልክ አግኝቷል።

ወይዘሮ መሰለች ዋና ፎቶው በማኅበራዊ ሚዲያ የሚዘዋወረው ወጣት እናት ናቸው። ስሙ ባንተ ዓለም ሰይድ እንደሚባልና የ23 ዓመት ታዲጊ ነው ልጄ አሉን።

ዘንድሮ የ12ተኛ ክፍል ተማሪ እንደኾነ እና ትምህርቱን አቋርጦ ከሦስት ወራት በፊት መጥፋቱንም ጨምረዋል።

በወቅቱ ከቤተሰብ ጋር አለመግባባት መፍጠሩን እና መጠነኛ የጤና ችግር የነበረበት መኾኑን ጠቅሰዋል።

በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨውን መረጃ አይተው ልጇቸውን ፍለጋ ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጥቁር ውሃ (አሮሚያ ክልል ሀዋሳ መግቢያ አካባቢ) አሁን ወላይታ ደርሰዋል። እስካኹን ግን ልጃውን እንዳላገኙም ገልጸዋል።

ልጃቸውን አግኝተው ወደ ፀበል ቦታ ለመውሰድ ያሰቡት ወይዘሮ መሰለች ያለበትን የሚያውቅ እንዲያግዛቸው ጠይቀዋል።

ከዚህ ውጭ ግን የባንክ ቁጥር በማኅበራዊ ሚዲያ እንዳላሰራጩ እና የገንዘብ ድጋፍም እንዳልጠየቁ ገልጸዋል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበዚህ ዓመት 8 ቢሊዮን ችግኞች ይተከላሉ።
Next article🕯”በኤሌክትሪክ ኀይል ችግር ምክንያት ወደ ትናንቱ ዘመን መመለስ የለብንም” የበየዳ ወረዳ ነዋሪዎች