የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 08/2018 ዓ.ም ይጀመራል።

9

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 08/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ባስተላለፈው የምክክር ተሳትፎ ጥሪ እንደገለጸው በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ እንዲሁም በውጪ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ጋር ያለመግባባት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በሕዝባዊ ውይይት ሰብስቦ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክረሃሳብ የሚያሰናዳበትን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 08/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

መላ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ታሪካዊ ኹነት መሳካት ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቀውን ሁሉ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉም ኮሚሽኑ ጥሪ አቅርቧል፡፡

በዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለመሳተፍ የተመረጡ የማኅበረሰብ ክፍሎች እና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ የሚችሉበትን ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ ኮሚሽኑ አሳስቧል፡፡

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከስምምነቱ በኋላ ነዳጅ ወደ ሁሉም አቅጣጫ በነጻነት ይጓጓዛል” ዶናልድ ትራምፕ
Next articleየጥጥ ምርት በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን።