የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ ማድረግ ጀመረ።

13

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀደም ሲል ባስታወቀው መሰረት ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚያደርገውን የቅድመ ምረቃ በረራ ዛሬ በይፋ መተግበር ጀምሯል።

በረራው በአካባቢው ነዋሪዎች፣ ተጓዦች እና የአየር መንገዱ ሠራተኞች ዘንድ ከፍተኛ ደስታ ፈጥሯል።

በመጀመሪያው በረራ የተሳፈሩ ተጓዦች አዲሱ አገልግሎት ለከተማው እና ለአካባቢው ሕዝብ ትልቅ እፎይታ እንደሚያመጣ ገልጸዋል።

“ከዚህ በፊት ለአየር ጉዞ ወደ ባሕር ዳር መጓዝ ይኖርብን ነበር። አሁን ግን ከደብረ ማርቆስ በቀጥታ መጓዝ መቻላችን ጊዜን እና ወጪን ይቆጥባል” ሲሉ ተጓዥ ተናግረዋል።

በበረራው ላይ የተሳተፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች በበኩላቸው ደብረ ማርቆስን በአየር መንገዱ የበረራ መዳረሻዎች ዝርዝር ውስጥ ማካተት የተቋሙ የአገልግሎት ማስፋፊያ አካል መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ በረራ ለአካባቢው ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለንግድ እና ለልማት እንቅስቃሴዎችም አዲስ እድል ይፈጥራል።

በቅድመ ምረቃ በረራው የተገኘው ስኬት ደብረ ማርቆስ ወደ ሀገሪቱ የአየር ትራንስፖርት አውታረ መረብ በይፋ የምትቀላቀልበትን አዲስ ምዕራፍ እንደሚያመላክት ተገልጿል።

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዳኝነት ነፃነት እና ተጠያቂነት ሚዛናዊነቱን ጠብቆ እንዲተገበር የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ያስፈልጋል።
Next article“ኢትዮጵያ በጤና ምርምር እና ትምሀርት ዘርፍ እያከናወነች ያለችው ሥራ ለአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚኾን ነው” የጎረቤት ሀገራት የሕክምና ተማሪዎች