የዳኝነት ነፃነት እና ተጠያቂነት ሚዛናዊነቱን ጠብቆ እንዲተገበር የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ያስፈልጋል።

8

 

አዲስ አበባ: ሰኔ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዓመታዊውን የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ኪያር ዘንድሮ ለሦሥተኛ ጊዜ የሚካሄደው ዓመታዊ የባለድርሻ አካላት ውይይት በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ ፍርድ ቤቶች የሕዝብ አመኔታ የሚታይባቸው ተቋማት ኾነው እንዲገነቡ ለማስቻል ነው ብለዋል።

ተቋሙ የሥራ ቦታዎችን ለተገልጋይ ምቹ የማድረግ እና በጠቅላይ ፍርድ ቤቶች የተጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ሥራ የማስቀጠል ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት መጓደል በተለያዩ መመዘኛዎች ውስንነት የታየበት መኾኑን ጠቁመዋል። ይህንን መነሻ በማድረግም ለመጀመሪያ ጊዜ የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ኮሚቴ በማቋቋም ክፍተቶችን የመለየት እና የዳኝነት አገልግሎቱን ፍትሐዊ እና ወጥ ለማድረግ የሚያስችሉ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።

የዳኝነት ነፃነት እና ተጠያቂነት ሚዛናዊነቱ ተጠብቆ እንዲተገበር የድህረ ውሳኔ መዛግብት ምርመራ ግኝት ሪፖርት ማድረግ እና ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት ወሳኝ ነውም ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የፍትሕ አካላት፣ የጠበቆች ማኅበራት ተወካዮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ የድህረ ውሳኔ ጥናት ሰነድ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበትም ነው።

#አሚኮ_ዜና #ፍርድ_ቤት #አዲስ_አበባ #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ፦ቤተልሄም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleአሁን ያለው ወጣት ታሪክ ተቀባይ ብቻ ሳይኾን ታሪክ ሠሪም ነው።
Next articleየኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የቅድመ ምረቃ በረራ ማድረግ ጀመረ።