
የፌዴራል መንግሥት እና ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን በፕሪቶሪያ በደረሱት የሰላም ስምምነት መሰረት የፌዴራሉ መንግስት የገባው ቃል መፈፀሙን የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አረጋዊ በርሔ (ዶ.ር) ለአሚኮ ገልጸዋል።
የኢፌዴሪ መንግሥት ስምምነቱን በማክበር ተቋርጠው የነበሩ የመሠረተ ልማቶችን ወደ ሥራ አስገብቷል።
በዚህም መንግሥት የትግራይን እናቶች ከተደጋጋሚ ለቅሶ ለመታደግ ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል፣
ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን ግን የስምምነት ቃሉን ሳያከብር ሀገርን ለማፍረስ እየሠራ ይገኛል ሲሉ አረጋዊ በርሔ (ዶ.ር) ተናግረዋል።
ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የፈረመው የሰላም ፍላጎት ኖሮት ሳይኾን፣ በጦርነቱ የደረሰበትን ሽንፈት እና ኪሳራ ጊዜ ለመግዛት መኾኑን ዓለም በግልጽ አውቆታል ነው ያሉት።
ሕገወጡ የሕወሃት ቡድን ሀገር የማፍረስ ተልዕኮው እንዲቆም በትግራይ እየተካሄደ የሚገኘው እምቢተኝነት ተጠናክሮ ቀጥሏል፣ መንግሥትም ሕገ መንግሥታዊ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ኀላፊነቱን እንዲወጣ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ መሥራች እና ሊቀመንበር አረጋዊ በርሄ (ዶ.ር) ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ: ኢብራሂም መሃመድ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
