“በወልድያ ከተማ የተሠራው ልማት የውበት ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚ እና የትውልድ ግንባታ ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

11

 

ወልድያ: ሰኔ 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ክልላዊ የኮሪደር ልማት ግምገማ እና የልምድ ልውውጥ በወልድያ ከተማ እያካሄደ ነው።

በወልድያ ከተማ እየተካሄደ ባለው መድረክ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አሥተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ ሞላ መልካሙ (ዶ.ር) እና በአማራ ክልል ከአርባ ከተማዎች የተሠባሠቡ ከንቲባዎች እና የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊዎች ተሳታፊ ናቸው።

በመድረኩ መክፈቻ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማት ዘርፍ አስተባባሪ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) በጸጥታ ችግር ውስጥ እንዳለች ተደርጋ የምትገመተው ወልድያ ከተማ የልማት እና የኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ ተምሳሌት ኾና አግኝተናታል ብለዋል።

ለዚህ ውጤት መብቃት ቁልፉ የመሪዎች እና የሕዝብ መናበብ መኾኑን ነው ያስረዱት።

ወልድያ ከተማ የተሠራው አጠቃላይ ልማት የውበት ብቻ ሳይኾን የኢኮኖሚ እና የትውልድ ግንባታ ነው ብለዋል።

የወልድያን ተሞክሮ በዐይን ቃኝተን መሰከርን ያሉት ዶክተር አሕመዲን በክልል ደረጃ ከተሞችን ለነዋሪዎቹ ምቹ እና ጽዱ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መኾኑን ነው ያስረዱት።

የወልድያን ተሞክሮ በማስፋት ከኅብረተሰቡ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጋር የተሳሰረ ልማት ሊሠራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

#አሚኮ_ዜና #የኮሪደር_ልማት_ወልድያ #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ 🇪🇹

ዘጋቢ፦ ካሳሁን ኀይለሚካኤል

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleልማትን ከኅብረተሰብ ተጠቃሚነት ጋር አስተሳስሮ በመሥራት ወልድያ ተሞክሮ ኾናለች።
Next article“ለሕዝብ ሰላም እና ልማት የሚተጉ ወጣቶች የሀገር መሠረቶች ናቸው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ