የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማሳደግ ይገባል።

19

 

አዲስ አበባ: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት በዘላቂነት እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ ላይ ያተኮረ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ የመክፈቻ መርሐግብር ተካሂዷል።

በኮንፍረንሱ ከ16 ሀገራት የተውጣጡ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ኮንፍረንሱ በዘርፉ ያሉ ባለሙያዎችን፣ ተመራማሪዎችን እና አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚያስተዋውቅ መኾኑን የኢፌዴሪ ቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር (ዶ.ር) ገልጸዋል።

የኮንፈረንሱ ዋና ዓላማ የቴክኒክ እና ሙያ ሥልጠና ተቋማት ለሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ሽግግር የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማሳደግ፣ በምርምር እና በቴክኖሎጂ ፈጠራ መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር መኾኑን የገለጹት ደግሞ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተሻለ መሬቻ (ዶ.ር) ናቸው።

ይህ ኮንፈረስ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ሽግግር ሂደት ውስጥ የቴክኖሎጂ አቅሟን ለማሳደግ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመኾን የያዘችውን ዕቅድ ለመደገፍ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላትም ገልጸዋል።

በዝግጅቱ ላይ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች የፈጠራ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሏል። ኮንፍረንሱ ዛሬን ጨምሮ ለሦሥ ተከታታይ ቀናት የሚቀጥል መኾኑ ተመላክቷል።

#አሚኮ_ዜና #የቴክኒክ_ሙያ_ተቋማት_ለኢንዱስትሪ_ልማት #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleመሬት የሰጠው የፍራፍሬ ሲሳይ! 🍊
Next articleኢራን ግጭት ለማርገብ ያስችላሉ ያለቻቸውን ቅድመ ኹኔታዎች አስቀመጠች።