
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እና የቀጣናውን ግጭቶች ለማስቆም የሚያስችል አዲስ የሰላም ስምምነት ማዕቀፍ መዘጋጀቱን የኢራን መገናኛ ብዙኀን ዘግበዋል።
የሁለቱ ሀገራት ተደራዳሪዎች በተለያዩ ግንባሮች ያሉ ጠላትነቶችን ሊያቆም የሚችል ረቂቅ ሰነድ አዘጋጅተዋል። እስካሁን ግን ምንም አይነት ይፋዊ እና የመጨረሻ ስምምነት ላይ አልተደረሰም።
ኢራን ለአሜሪካ ባቀረበችው የጽሑፍ መግባቢያ ሰነድ ረቂቅ:-
👉 ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም የቀጣናው ግንባሮች ላይ አስቸኳይ እና ቋሚ የተኩስ አቁም ማወጅ
👉 በ30 ቀናት ውስጥ ሁሉንም አይነት የባሕር ላይ የትራንስፖርት እና የንግድ እገዳዎችን ማንሳት
👉 በ30 ቀናት ውስጥ ወሳኝ የኾነውን የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ መልሶ መክፈት፤ ኢራን ወሽመጡን የመቆጣጠር መብቷን እንደምታስቀጥልም አካታለች
👉 በኢራን የነዳጅ እና የፔትሮኬሚካል ምርቶች ላኪነት ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን በጊዜያዊነት ማንሳት
👉 በተለያዩ የዓለም ባንኮች የታገደውን 24 ቢሊዮን ዶላር የኢራን ሀብት መልቀቅ
👉 አሜሪካ በኢራን የውስጥ የፖለቲካ ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ እንደማትገባ ማረጋገጫ እና ቃል መግባት የሚሉትን በማካተት ማቅረቧን አስታውቃለች።
በሁለቱ ሀገራት መካከል የታየው ያልተጠበቀ የግንኙነት መሻሻል በቀጣናው ላይ ትልቅ የጂኦፖለቲካ ለውጥ ሊያመጣ እንደሚችል ቢነገርም ከዋሽንግተን በኩል እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ ምላሽ የለም።
#አሚኮ_ዜና #የውጭ_የአሜሪካ_ኢራን_ድርድር
ዘጋቢ፦ስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
