👁️🩺 የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነፃ የዐይን ሞራ ግርዶሽ የቀዶ ጥገና ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው።

12

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ”ላይት ፎር ዘ ወርልድ” ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ነፃ የዐይን ሕክምና እና የዐይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ሕክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

​ሆስፒታሉ ለማኅበረሰቡ ያለውን የጤና አገልግሎት የመስጠት ኀላፊነት በተግባር እያሳየ ሲኾን በዚህም በባሕር ዳር ከተማ እና አካባቢዋ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የዐይን ጤናቸውን እንዲጠብቁ የሚያስችል ዘመቻ አዘጋጅቷል።

​የሆስፒታሉ የዐይን ሕክምና ክፍል አስተባባሪ ድረስ ዓለማየሁ ዘመቻው ከሰኔ 8/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነው ብለዋል። ማንኛውም የዐይን ችግር ያለበት የማኅበረሰብ ክፍል ወደ ሆስፒታሉ በመምጣት ተጠቃሚ መኾን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ለታካሚዎች አስፈላጊው የሕክምና ምርመራ፣ የመድኃኒት አለያም የቀዶ ጥገና አገልግሎት በነፃ ይሰጣል ነው ያሉት።
ከፍተኛ የዐይን ችግር ያለባቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመለየትም ሕክምና እና መድኃኒት እንዲያገኙ ይደረጋልም ብለዋል።

​ስለዚህ ማንኛውም የዐይን ሕመም ችግር ያለባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ከሰኔ 8/2018 ዓ.ም እስከ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ወደ ፈለገ ሕይወት አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሄድ አገልግሎቱን እንዲያገኙ ጥሪ አስተላልፈዋል።

#አሚኮ_ዜና #የዐይን_ቀዶ_ሕክምና #ባሕር_ዳር #አማራ #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🏭 ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከስኳር ምርት ባሻገር !
Next articleመሬት የሰጠው የፍራፍሬ ሲሳይ! 🍊