
ባሕር ዳር: ሰኔ 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ከ24 ሺህ በላይ ሄክታር መሬት ላይ ያረፈ ግዙፍ የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት ነው።
🚜 🌱ፋብሪካው በዋናነት ስኳር እና የስኳር ተረፈ ምርቶች ላይ ዓላማ አድርጎ የተቋቋመ ቢኾንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ከስኳር ማምረት ጎን ለጎን ሰፊ የግብርና ልማቶችንም እያለማ ይገኛል።
የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የሕዝብ ግንኙነት እና ተሳትፎ ኀላፊ አድገህ መኩሪያ ለአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ እንደገለጹት ፋብሪካው ከአገዳ ልማቱ በተጨማሪ የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማቶችንም እያለማ ይገኛል።
🍊🍌የአካባቢውን ጸጋ በመጠቀም ብርቱካን፣ ሙዝ፣ ሀባብ፣ ሽንኩርት እና ሌሎችንም የአትክልት እና ፍራፍሬ ዓይነቶች በስፋት በማምረት ለገበያ እያቀረበ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
🐄 በእንስሳት ሃብት ልማትም በወተት ልማት እና በንብ እርባታ ሥራዎች በመሣተፍ ለአካባቢው ማኅበረሰብ ጭምር የተሞክሮ ማዕከል በመኾን ለፋብሪካውም ተጨማሪ የገቢ ማስገኛ እንዲኾን እየተሠራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በቅርቡ ወደ ምርት መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል።
#አሚኮ #ጣናበለስ #ልማት #ኢትዮጵያ🇪🇹
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
