
አዲስ አበባ: ሰኔ 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “በአጀንዳ ልየታ ዝግጅት የፓርቲዎች ሚና” በሚል መሪ መልዕክት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ ክልሎች ከተውጣጡ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ሀገር አቀፍ የአጀንዳ ልየታ መርሐግብርን በአዲስ አበባ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ በኢትዮጵያ እጅግ መሠረታዊ እና ሀገራዊ በኾኑ ጉዳዮች ላይ አለመግባባቶች የረዥም ጊዜ ታሪክ ያላቸው ናቸው ብለዋል።
እንደ ሀገር በአንፃራዊነት ነፃ እና ገለልተኛ የምክክር ሂደትን ማስተባበር የሚያስችል አቅም መፈጠሩን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ተናግረዋል።
በምክክር ሂደቱ እንዲሳተፉ የተወከሉ ተሳታፊዎች በአጀንዳ ልየታ መሳተፋቸውን ገልጸዋል።
ከሀገር ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በሂደቱ በማሳተፍ የአጀንዳ ልየታ ሥራ መሠራቱን የጠቀሱት ዋና ኮሚሽነሩ በጥቅሉ በዚህ ሂደት የሃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ ምሁራን፣ ሠራተኞች እና የዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ ተሳትፈዋል ብለዋል።
በቀጣይም ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤን በቅርቡ የሚጀምር መኾኑን ገልጸው የሚቀጥለው ሥራም የምክክር አጀንዳዎችን መቅረጽ እና ተደራሽ ማድረግ፣ አማካሪዎችን ዝግጁ ማድረግ፣ የሎጂስቲክ ሥራዎችን ማጠናቀቅ እና የፖለቲካ ተዋናዮችን ተሳትፎ አጠናክሮ ማስቀጠል ነው ብለዋል።
ለሂደቱ መሳካት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሁሉን አቀፍ ዝግጅት እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ጥሪ አቅርበዋል።
#አሚኮ_ዜና #ሀገራዊ_ምክክር_ኢትዮጵያ
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
