
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ ራስ ዓሊ ከተማ፣ የየጁዎች ሥልጣኔ መገኛ፣ የአራቱ አውራ መንገዶች መገናኛ፣ ተራሮች እንደ ሐረግ ከተጋመዱባት፣ የሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ ንግድ ማዕከል በሆነችው የጥንቷ ገነቴ፣ የአሁኗ ወልድያ ከተማ ገብተናል ሲሉ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
“ጎበዝና ቆንጆ ከሚወለዱባት፣ ታሪክና ትውፊት ከተከማቸባት፣ ከመስጠት በስተቀር ስስት ከሌለባት ወልድያ ስንደርስ በአካባቢው ወግ መሰረት ደማቅ አቀባበል ላደረጉልን ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ ለካቢኔያቸው፣ ለወልድያ ከተማ ከንቲባ እና ለከተማዋ ነዋሪዎች ከልብ የመነጨ ምስጋና ለማቅረብ እወዳለሁ” ብለዋል።
በወልድያ በሚኖራቸው ቆይታም የተለያዩ የልማት ሥራዎችን እንደሚጎበኙ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
