ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ ጸደቀ።

13

 

አዲስ አበባ: ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 24ኛ መደበኛ ሥብሠባው የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርት እና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሠብሣቢ ዲማ ነገዎ (ዶ.ር) ረቂቅ አዋጁ የሕግ እና የፖሊሲ ክፍተትን በመሙላት እና የሀገሪቱን መረጃ እና ደኅንነት ውጤታማ በማድረግ የፋይናንስ ደኅንነትን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።

የተሻሻለው ረቂቅ አዋጅ የሀገሪቱን የሳይበር ደኅንነት አዋጅ ለማረጋገጥ ያግዛልም ነው ያሉት።

የሳይበር ደኅንነት ፕሮግራሞችን ለማስፈጸም፣ ለሥልጠና፣ ለምርምር እና ለቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ የሚውል ራሱን የቻለ የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደኅንነት ፈንድ በአዋጁ በአዲስ ምዕራፍ መደንገጉንም አስረድተዋል።

የሳይበር ደኅንነት ረቂቅ አዋጅ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የወጣ ሲኾን በተለይም የዜጎች የመረጃ እና ደኅንነት መገልገያ ተቋማት ላይ ትኩረት የሚያደርግ መኾኑን የቋሚ ኮሚቴው ሠብሣቢ አብራርተዋል።

የሳይበር ደኅንነት አዋጅ በሀገር ውስጥ ባሉ ቁልፍ ተቋማት እና ከሀገር ውጭ ባሉ የሀገሪቱ መሠረተ ልማት ላይ ተፈፃሚ እንደሚኾንም ተደንግጓል ብለዋል።

የሳይበር ደኅንነት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ ለሀገር ደኅንነት እና ሰላም አስፈላጊ መኾኑን ያመነው ምክርቤቱ ረቂቅ አዋጁን በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

#አሚኮ_ዜና #የሳይበር_ደኅንነት_ማሻሻያ_ረቂቅ_አዋጅ _ኢትዮጵያ

ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኀይል መቆራረጥን ለማስቀረት እየሠራ ነው።
Next articleየማዕድን ሀብትን በሳይንሳዊ ዕውቀት እና በዘላቂነት ለመጠቀም ጥናትን እንደ ድልድይ መጠቀም ይገባል።