“የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትግበራ እውቅና የሚሰጠው ነው” የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም

15

 

አዲስ አበባ፡ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም(አሚኮ) ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ ባለፉት ዓመታት ያከናወነቻቸው ተግባራት በአካባቢ ጥበቃ የመሪነት ሚናዋን ይበልጥ ያጎላ መኾኑን የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም አስታውቋል።

የፕሮግራሙ የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሳሙኤል ግባይዴ (ዶ.ር)
ሀገሪቱ ባለፉት ሰባት ዓመታት 50 ቢሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን በመትከል የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ማከናወኗ የላቀ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ይህንን ትልቅ ዕቅድ በማሳካት በዓለም ደረጃ ተዓምር ሠርታለች ነው ያሉት።

አረንጓዴ ኢኮኖሚ መተግበሯ ሀገሪቱ አፍሪካን ወክላ የዓለም ሀገራት የሚሳተፉበትን እና ታላቅ አጀንዳ የኾነውን የCOP32 ጉባዔን ለማስተናገድ እንድትመረጥ አስችሏታል ብለዋል ቋሚ ተወካዩ።

“ሀገሪቱ ባለፉት ዓመታት ላከናወነቻቸው ተግባራት ተቋማችን እውቅና ይሰጣል” ብለዋል የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሳሙኤል ግባይዴ (ዶ.ር)።

ዘጋቢ፦ ኢብራሒም መሐመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኀይል መቆራረጥን ለማስቀረት እየሠራ ነው።