“ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

15

 

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ መጎብኘታቸውን ገልጸዋል። በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ሕትመት (3D printing)፣ የቅድመ ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው ነው ያሉት።

እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሠርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

‎ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው ብለዋል። “ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ሥራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን እድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል” ሲሉም በመልእክታቸው አስፍረዋል።

#አሚኮ #አማራ #ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ወልድያ የተራራ ሥር ጌጥ፤ የኮረብታ ግርጌ ፈርጥ”
Next article“የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትግበራ እውቅና የሚሰጠው ነው” የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም