
ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሣተፉ በመራጭነት መመዝገቡ ይታወቃል። በመሆኑም በካምፖቹ በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ የመስጠት ሂደት በነገው ዕለት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከናወን ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ መስጠት ሂደት እንዳስፈጸመ ይታወቃል። በአሁን ሰዓት ቦርዱ ከምርጫ ክልል ጽሕፈት ቤት ወደ ቦርዱ ማዕከል በመምጣት ላይ ያሉ ውጤቶችን የማረጋገጥ ፣ የኦዲት ግኝት ያለባቸውን ውጤቶች የመመርመር እንዲሁም የተረጋገጡ ውጤቶችን ወደ መረጃ ቋት በማስገባት እና በፖለቲካ ፓርቲዎችና በግል ዕጩዎች የቀረቡ አቤቱታዎችን በሕግ ባለሙያ ጉባዔ አማካኝነት የማደራጀትና ምሥክር የመሥማት ሥራ ላይ ያለ ሲሆን፤ በቀጣይም በተጠቀሰው ሂደት ያለፉ ውጤቶች ለቦርድ ውሣኔ በማቅረብ እና በማፀደቅ በሕጉ መሠረት ለሕዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል።
ቦርዱ “በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17” በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም የካምፑ ነዋሪዎችን በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ እንዲሣተፉ በመራጭነት መመዝገቡ ይታወቃል።
በመሆኑም በካምፖቹ በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፅ የመስጠት ሂደት በነገው ዕለት ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚከናወን ይሆናል። መረጃው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
