የሐረሪ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት ውሳኔዎች።

13

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የሐረሪ ክልል መሥተዳድር ምክር ቤት በተለያዩ መዋቅራዊ እና ማኅበራዊ ረቂቅ አዋጆች እና ደንቦች ላይ ከተወያየ በኋላ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

ካቢኔው ካጸደቃቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች መካከል የክልሉን ብዙኅን መገናኛ ኤጀንሲ በአሁኑ ወቅት ከደረሰበት የዕድገት ደረጃ ጋር ለማጣጣም “የሐረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ” በሚል ስያሜ እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

በሰው መነገድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያስችለውን የፍልሰት ጉዳዮች አስተባባሪ ምክር ቤት እና የትብብር ጥምረት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብንም በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በክልሉ የተበታተኑ አሠራሮችን በማስቀረት ፍትሐዊ፣ ጥራት እና ቀጣይነት ያለው የጤና አገልግሎትን ለኅብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እና ግልጽ የፋይናንስ ተጠያቂነትን ለመዘርጋት የወጣውን የጤና መድኅን ማሻሻያ ረቂቅ ደንብ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በዩኔስኮ የተመዘገቡትን ሁለት ታላላቅ ቅርሶች ጨምሮ የክልሉን በርካታ ቁሳዊ እና መንፈሳዊ ቅርሶች በባለቤትነት ለመምራት፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን ለማልማት እና ለዘርፉ የበጀት እና የሰው ኀይል ነፃነት ለመስጠት የወጣውን የቱሪዝም ኮሚሽን ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ በሙሉ ድምጽ አጽድቆ ወደ ሥራ እንዲገባም አድርጓል።

#አሚኮ_ዜና #የሐረር_መሥተዳደር_ምክር_ቤት #አዋጆችን_ማጽደቅ_ኢትዮጵያ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🌿 ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች የነገው ትውልድ ህልውና ናቸው።
Next articleየፍኖተ ሰላም ከተማ አሥተዳደር ለ92 የቤት ማኅበራት የእጣ ማውጣት ሥነ ሥርዓት አካሂዷል::