🌿 ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች የነገው ትውልድ ህልውና ናቸው።

11

​
​ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬታማ ለማድረግ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እየሠራ ነው።

ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራ ከሚከናወንባቸው አካባቢዎች መካከል የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ተጠቃሽ ነው።

የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ አዲሱ ስማቸው ለሚከናወነው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ቦታዎችን የመለየት እና ችግኞችን የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።

🌿 እንደ ብሔረሰብ አሥተዳደር 111 ሚሊዮን በላይ የተለያዩ የደን፣ የመኖ እና የፍራፍሬ ችግኞች ለማዘጋጀት ታቅዶ እየተከናወነ እንደኾነ መምሪያ ኀላፊው ተናግረዋል። ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ለተከላ ተለይቷልም ብለዋል።

​ለኅብረተሰቡ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም የሚሰጡ የፍራፍሬ ችግኞች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ነው ያሉት።

🥑 የአቮካዶ፣ የቡና እና የፓፓያ ሰፋፊ ክላስተሮችን ለማዘጋጀት ታቅዷልም ብለዋል። ለዚህም የሚኾን 2 ነጥብ 68 ሚሊዮን ችግኝ ለማልማት ዝግጅት ተደርጓል ነው ያሉት።

👉 የተከላው ሥራ ስኬታማ እንዲኾን እና የችግኞችን የጽድቀት መጠን ለማሳደግ፣ ተስማሚ የኾኑ ቦታዎችን የማዘጋጀት ሥራ እየተሠራ እንደኾነም አንስተዋል።

👉 ለተከላ የደረሱ ችግኞችን የማዘጋጀት እና ማኅበረሰቡን ባለቤት የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል ኀላፊው።

​የባለፈው ዓመት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የተመዘገበው የችግኞች የጽድቀት መጠን ከ87 በመቶ በላይ መኾኑን ነው የተናገሩት።

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ስኬታማ ለማድረግ ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።

👉 እንደ ቢሮ ኀላፊው ገለጻ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች ትኩረት በመስጠትም እየተሠራ እንደኾነ ነው የተናገሩት።

🌱 1 ነጥብ 78 ቢሊዮን ችግኞች ለማዘጋጀት ታቅዷል ብለዋል።
🌱 እስካሁን 1 ነጥብ 72 ቢሊዮን (97 ነጥብ 3 በመቶ) ችግኞች ተዘጋጅተዋል።
🌱 ከ261 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት የተከላ ቦታ ተለይቶ የችግኝ መትከያ ጉድጓድ ዝግጅት ሥራ በቅንጅት እየተከናወነ ይገኛል ነው ያሉት።

የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭ በሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት እና በኅብረተሰቡ የሥራ ባሕል ላይ ከፍተኛ ለውጥ ማምጣቱንም ኀላፊው አንስተዋል።

ማኅበረሰቡ የሥራው ዋና ባለቤት እየኾነ ነው ያሉት ኀላፊው ችግኞችን በመንከባከባቸው ቀደም ሲል የተተከሉ ችግኞች የመጽደቅ መጠን በእጅጉ ከፍ ብሏል ነው ያሉት።

“ዛሬ የሚተከሉ ችግኞች የነገው ትውልድ ኅልውና እንደኾኑ ነው” የገለጹት።

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየዢ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ መግባትና አንድምታው።