
ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሰሜን ኮሪያ ገብተዋል። በፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
የዢ ጉዞ የዚህ ዓመት የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ጉብኝት ነው። ጉዞው የተደረገው የሩሲያውን መሪ ቭላድሚር ፑቲንንና የአሜሪካውን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን በቤጂንግ ካስተናገዱ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መኾኑን ሲኤን ኤን ዘግቧል።
ቻይና ከፒዮንጊያንግ ጋር ያላትን የቆየና ታሪካዊ የቅርብ ግንኙነት በድጋሚ ለማረጋገጥ ጉብኝቱ ትልቅ ፋይዳ አለው።
በቅርብ ዓመታት ውስጥ የኪምና የፑቲን ግንኙነት እያደገ ቢመጣም ቻይና አሁንም ለሰሜን ኮሪያ እጅግ ወሳኝ የኢኮኖሚ የሕይወት መስመርና ዲፕሎማሲያዊ አጋር መሆኗን ቤጂንግ ያሳየችበት ግልጽ ምልክት ተደርጎ ይወሰዳል።
ዢ ከጉዞው አስቀድሞ ለሰሜን ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን በላኩት ደብዳቤ ላይ “ዘመናት ቢቀያየሩም ወይም ዓለም አቀፋዊው ሁኔታ እንዴትም ቢለዋወጥ፣ በቻይና እና በሰሜን ኮሪያ መካከል ያለው ባህላዊ ወዳጅነት የማይበጠስ፣ ዘላቂና ሁልጊዜም ሕያውነትን የሚያንጸባርቅ ነው” ብለዋል።
ለሰሜን ኮሪያ የቤጅንግ ጉብኝት በሩሲያና በቻይና መካከል ለረጅም ጊዜ ስታደርግ የነበረውን የኃይል ሚዛን የመጠበቅ አካሄድ ሌላ ምዕራፍ ነው። ይህም ከአንዱ ወገን ላይ ብቻ ከመጠን በላይ ጥገኝነት እንዳይኖራት በማድረግ ከሁለቱም ወገን ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን ለማግኘት የምትጥርበት ዘዴ ነው በሚልም ተጠቁሟል።
ሁለቱ መሪዎች በቆይታቸው ዓለማቀፋዊና የሁለትዮሽ ግንኙነቶቻቸው ላይ ይመክራሉ።
በስማቸው አጥናፍ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
