“እውነተኛ እና ዘላቂ እድገት ሊመጣ የሚችለው ከአካባቢ ጥበቃ ጋር የተሳሰረ ሥራ መሥራት ሲቻል ነው” አቶ ተስፋሁን ዓለምነህ

18

 

ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዓለም አቀፍ የአካባቢ ቀንን “የአየር ንብረት ተጽዕኖን መግታት ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ መልዕክት የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት እያከበረ ይገኛል።

የአማራ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኀላፊ ተስፋሁን ዓለምነህ ዓለም አቀፍ የአካባቢ ቀን በዓለም ለ53ኛ፤ በኢትዮጵያ 33ኛ፤ በክልል ደረጃ ደግሞ ለ29ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል ብለዋል።

አላማውም የአየር ንብረት ለውጥን መከላከል፤ ምርታማነትን ማሳደግ፤ የውኃ አካላትን እና የብዝሃ ሕይወትን መጠበቅ እንደኾነ ገልጸዋል።

የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ የአንድ ክልል ወይም ሀገር ብቻ ሳይኾን መላውን ዓለም የሚያስተሳስር ዓለም አቀፋዊ አጀንዳ ነው ብለዋል። የሚሠራው ማንኛውም የአካባቢ ጥበቃ ሥራ ውጤቱ ለአጠቃላይ ዓለም የሚተርፍ እንደኾነ ነው የገለጹት።

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ ልማትን ከአካባቢ ጥበቃ ጋር አሥተሣሥሮ መሥራት ያስፈልጋል ነው ያሉት። በክልሉም የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በትኩረት እየተሠራበት መኾኑን አንስተዋል። የደን ሽፋንን ማሳደግ ተችሏልም ነው ያሉት።

ደኖችን በመጠበቅ፣ ውኃን በመንከባከብ እና የአፈር ብክለትን በመከላከል ረገድ በተግባር መሥራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

#አሚኮ-ዜና #አካባቢ-ጥበቃ #አማራ #ኢትዮጵያ🇪🇹

ዘጋቢ፦ ሥራውድንቅ ደሳለው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የአካባቢውን ነዋሪዎች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።
Next articleየዢ ጂንፒንግ ሰሜን ኮሪያ መግባትና አንድምታው።