
ባሕር ዳር: ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ✍️ራስን ማግለል እና ከመጠን ያለፈ ሚስጥራዊነት፦
-በርን ዘግቶ ለረጅም ሰዓታት ስልክ ወይም ኮምፒውተር መጠቀም
-ስልኩን ሌላ ሰው እንዳይዝባቸው መሳቀቅ ወይም መቆጣት
-ኦንላይን ላይ የሚያወራቸውን ሰዎች ማንነት በሚስጥር መያዝ
✍️ማኅበራዊ ለውጦች፦
-ከቀድሞ ጓደኞች፣ ከቤተሰብ ጨዋታዎች እና ግንኙነቶች ሙሉ በሙሉ መራቅ
-በትምህርት ላይ ፍላጎት ማጣት እና ውጤት መቀነስ።
✍️ስሜታዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ለውጦች፦
-ያለምንም ግልጽ ምክንያት በድንገት መበሳጨት፣ ቶሎ ማልቀስ ወይም ፍጹም ዝምተኛ መኾን
-ስልክ ከተጠቀሙ በኋላ ከፍተኛ ፍርሃት፣ ጭንቀት እና የጥፋተኝነት ስሜት ማሳየት
-የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ እንቅልፍ ማጣት እና በሕልም መቃዠት።
✍️እነዚህ ምልክቶች በታዳጊዎች ላይ ከታዩ በተረጋጋ ስሜት ቀርቦ ማናገር እንደሚመከር የኢንሳ መረጃ ይገልጻል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ!
https://linktr.ee/Amharamediacorporations
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
