ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብርን አስጀመሩ።

8

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በኮምቦልቻ ከተማ ተገኝተው አራተኛውን የአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል።

አራተኛው የአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር “ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት” በሚል መሪ መልዕክት ነው መካሄድ የጀመረው።

በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ ከርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በተጨማሪ ሌሎች ከፍተኛ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል።

በአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበት፣ ልምድ የሚለዋወጡበት እና የገበያ ትስስር የሚፈጥሩበት ኤክስፖ ተዘጋጅቷል። በኤክስፖው 145 አምራች ኢንዱስትሪዎች እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው እንዲጨምር አድርጓል። እንደማነቆ የሚያነሷቸው ችግሮችም እንዲፈቱ እያደረገ ነው።

#አሚኮ_ዜና #ኢትዮጵያ_ታምርት #አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article🏙 ኮሪደር ልማት ከከተማ ውበት በላይ የሥራ ባሕልን በእጅጉ እየቀየረ ነው ።
Next article“ተወዳዳሪ እና ቀዳሚ ለመኾን በቅንጅት እና በትብብር መሥራት አለብን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ