የአዲስ አበባ የወንዝ ዳርቻ ተግባራት የአካባቢ ጥበቃን እና ከኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጋር አጣምረው የያዙ ናቸው።

6

 

አዲስ አበባ: ግንቦት 29/2018 ዓ.ም (አሚኮ) ዓለም አቀፍ የአካባቢ ጥበቃ ቀን በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ “ጽዱ ኢትዮጵያን ባሕል እናድርግ” በሚል መሪ ሃሳብ ተከብሯል።

ቀኑ የተከበረው በአዲስ አበባ ከተማ በቅርቡ ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በይፋ ወደ ሥራ በገባው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን በመጎብኘት ነው።

የፌዴራል አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ለሊሴ ነሜ (ዶ.ር) በከተማዋ የተከናወኑ የወንዝ ዳርቻ ተግባራት ውበትን ከአካባቢ ጥበቃ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ጋር አጣምረው የያዙ ሥራዎች መኾናቸውን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም (ዩኤንዲፒ) የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሳሙኤል ግባይዴ (ዶ.ር) በበኩላቸው የወንዝ ዳርቻ ሥራዎች ሀገር በቀል ዕውቀት እና ዘመናዊነት ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተጣምረው የተሠሩ መኾናቸውን ተመልክቻለሁ ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎቿ ቀዳሚ ነች፤ ይህ ተግባሯ ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል በጋራ መሥራታችን ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በዕለቱ በአካባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሰማሩ
ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።

#አሚኮ_ዜና #የወንዝ_ልማት_አማራ_ክልል #ኢትዮጵያ

ዘጋቢ:- ኢብራሂም መሃመድ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ሚሊሻ የሰላም ምንጭ እና የሕግ መከታ ነው”
Next articleየአማራ ክልል “ኢትዮጵያ ታምርት” ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ነገ በኮምቦልቻ ከተማ ይካሄዳል።