🚫ታዳጊዎችን ዒላማ ያደረጉ አደገኛ የሳይበር ጥቃቶች፦

15

 

ባሕር ዳር: ግንቦት 28/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የበይነ መረብ ቴክኖሎጂን በመጠቀም በሕፃናት እና ታዳጊዎች ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች እጅግ ውስብስብ እየኾኑ ነው።

ከ3መቶ ሺ በላይ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች የመስመር ላይ ብዝበዛ እና ጥቃቶች ሰለባ መኾናቸውን ኢንሳ ጠቁሟል።

🚫ታዳጊዎችን ዒላማ ያደረጉ አደገኛ የሳይበር ጥቃቶች የትኞቹ ናቸው?

#በኢንተርኔት አማካኝነት የሚፈጸም የሕፃናት ማታለል (Cyber Grooming)፦ የሳይበር አዳኞች የሕፃናትን አቻ ዕድሜ በመምሰል፣ የሐሰት ወዳጅነት በመመሥረት እና እንዲታመኑ በማድረግ ሚስጥራቸውን ተቀብለው ለወሲባዊ ብዝበዛ የሚያዘጋጁበት አደገኛ ስልት።

#ሴክስቶርሽን (Sextortion)፡ አጥቂዎች ከልጆች ያገኙትን የራቁት ወይም ወጣ ያሉ ምስሎችን ተጠቅመው “የፈለግኩትን ካላደረጋችሁ ምስሉን እበትነዋለሁ” በማለት ታዳጊዎችን ለከፋ ሥነ-ልቦናዊ ጫና የሚዳርጉበት የጥቃት አይነት ነው።

#የማኅበራዊ ሚዲያ ትንኮሳ ወይም ጉልበተኝነት (Cyber Bullying)፡ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ታዳጊዎችን ስም ማጥፋት፣ ማሸማቀቅ እና የሚያንቋሽሹ መልዕክቶችን በመላክ ከፍተኛ የሥነ-ልቦና ቀውስ የሚፈጥር ነው።

#በኢንተርኔት አማካኝነት ሰዎችን መከታተል ወይም ማስፈራራት (Cyber Stalking)፦አጥፊዎች የሕፃናትን የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እና የሚሄዱባቸውን ቦታዎች (Location) በድብቅ እየተከታተሉ የሚያደርሱት የትንኮሳ አይነት ነው።

ልጆች ከእነዚህ አደጋዎች እንዲጠበቁ በንቃት መከታተል አስፈላጊ ነው።

የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይሁኑ

https://linktr.ee/Amharamediacorporations

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ምርምሮች የማኅበረሰቡን ችግር የሚፈቱ መኾን አለባቸው”
Next article“ኅብረተሰቡ በምርጫው ያሳየው ተሳትፎ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ትልቅ ተስፋ ነው” የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን